መጽሐፍ

በጉጉት የሚጠበቀው 'የመደመር ትውልድ' መጽሐፍ እየደረሰ ነው! ለኦንላይን ሽያጭ መቼ እንደሚቀርብ ለማወቅ እና ከመጀመሪያዎቹ አንባቢዎች አንዱ መሆንዎን ለማረጋገጥ፣ ኢሜል አድራሻዎን ያጋሩን። ይህን በማድረግ፣ መጽሐፉ የሚለቀቅበትን ቀን ጨምሮ ሁሉንም አዳዲስ ዜናዎችን ያገኛሉ።

የመደመር ትውልድ

 

ሀገር የምትገነባው ወይም የምትፈርሰው በትውልድ ቅብብል ነው።

ከተረከበው አብልጦ የሚሠራ ትውልድ ይገነባታል። ከተረከበው አሳንሶ የሚሠራ ትውልድ ያፈርሳታል።

ካለፈው ትውልድ በመማር፣ በዛሬው ትውልድ በመታገል፣ በነገው ትውልድ ላይ ደግሞ በመሥራት የተሻለች ሀገር መገንባት ይቻላል።

ጥያቄው እንዴት? የሚለው ነው።

የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ይሄንን ለመመለስ ይሞክራል።

 

መጽሐፉን ይግዙ

 

አሁን በድምፅ ትረካ የተዘጋጀውን #መደመር መጽሐፍ በነጻ ለማድመጥ ወይም ፋይሉን ለማውረድ ይችላሉ። ቢሻዎት ደግሞ፣ የመጽሐፉን ምዕራፎች ዕለታዊ ምንባብ በፋና ሬዲዮ እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ ያድምጡ።

 

መደመር የተሰኘው ይህ መጽሐፍ የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚና የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የሃገር መምራት ሃላፊነት ላይ ከመጡ በኋላ የጻፉት የመጀመሪያ መጽሐፋቸው ሲሆን፤ በይዘቱም ወቅታዊው የኢትዮጵያ የፖለቲካ መህዳር ሃገር በቀልና አዲስ የፖለቲካ አስተምህሮን ለማስተዋወቅ ታሪካዊ፣ ተግባራዊና አመክኔያዊ ገፊ ምክንያቶች ኢንደሚታዩበት ይሞግታል። እንደ መጽሐፉ የአዲስ ሃገር በቀል ፖለቲካዊ ርዕዮተአለም አስፈላጊነት የሚመነጨው ባለፈው ግማሽ ምዕተ-አመት በሃገራችን ወስጥ ከሌላው አለም እየተዋስን የሞከርናቸው ፖለቲካዊ አስተምህሮዎች የተባለላቸውን ያህል ውጤት ያላመጡበት አንዱ ምክንያት ለኢትዮጵያ ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች እንዲሁም ፖለቲካዊ ምህዳር ባዕድ መሆናቸው እንደሆነ ያስገነዝባል። በመሆኑም ይህን በሃገር ደረጃ የሚታይ በተውሶ ርዕዮተአለም የመዋለል ሃገራዊ ችግር ኢትዮጵያዊ ባህሎችንና ልማዶችን ተንተርሶ ሃገራዊ ችግርን የመፍታት አስፈላጊነትን በማጤን መደመርን እንደ ሃገር በቀልና አዲስ የፖለቲካ ርዕዮተ-አለማዊ አቅጣጫ ያመላክታል።

መጽሐፉ አራት ክፍሎች ያሉት ሲሆን በዓለም ላይ የሚቀነቀኑ የተለያዩ ፍልስፍናዎችን በመዳሰስ ለሀገር በሚጠቅም መልኩ ቁም ነገራቸውን በመቅሰም የራሳችን የምንለው ችግራችንን ሊፈታ የሚችል መላ ማመላከት ላይ እንድናተኩር ይጋብዛል። ለዚህም እንስካሁን የተለመደውን የተነጣጠሉ ትናንሽ አቅሞችን ከመገንባት ባለፈ በመደመር ትልቅ ሃገራዊ ወረት መፍጠርን ያበረታታል።

 

የአማርኛ መጽሐፍ ትዕዛዝ Order Afaan Oromo Book

 

አሁን በድምፅ ትረካ የተዘጋጀውን #መደመር መጽሐፍ በነጻ ለማድመጥ ወይም ፋይሉን ለማውረድ ይችላሉ። ቢሻዎት ደግሞ፣ የመጽሐፉን ምዕራፎች ዕለታዊ ምንባብ በፋና ሬዲዮ እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ ያድምጡ።

 

 

"የመጀመሪያው እና ትልቁ ልማት ሰላም ነው።"
"ዘረኝነት እና መከፋፈልን ከሀገራችን እናጥፋ፤ የተማረና በምክንያት የሚከራከር ዜጋ እንፍጠር።"
"ለሴቶች ክብር የማይሰጥ ማህበረሰብ ያልሠለጠነ ብቻ ሳይሆን ወደፊትም የማይሠለጥን ነው።"
"ጥበብ በባሕሪዋ የሚፈጥራትን ብቻ ሳይሆን ዐውቆ የሚጠቀምባትን ሕዝብ ትፈልጋለች።"
"ሞትን ማሸነፍ አይቻልም፤ በሕይወት ውስጥ ማሸነፍ የሚቻለው [ግን] ጥላቻን ብቻ ነው።"
"ድንበር ከጎረቤት ሀገራት ጋር እንጅ በአንድ ሀገር ውስጥ ሊኖር አይችልም።"

መደመር ለእርስዎ ምን ማለት ነው?

ውይይቱን ይቀላቀሉ። መደመር ለእርስዎ ለእርስዎ ምን ማለት እንደሆነ ለአለም አስተያየትዎን ለማጋራት በይነተገናኝ ገጹን ይጠቀሙ።

ውይይቱን ይቀላቀሉ